federal proclamations, regulations, directives, regional constitutions and laws.
You can search cases by number, volume, subject matter
Training and teaching materials, articles, legal forms, links to resources...
የማይንቀሳቀስ ንብረትን አስመልክቶ የሚቀርብ የመፋለም ክስ በይርጋ ቀሪ ነው (ቀሪ ሆኗል) ሊባል የሚችል ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1677 1845 1206 1188-1192
Download Cassation Decision
በቃል ከሥራ ተሰናበትኩ በሚል ክስ የሚያቀርብ ሠራተኛ አሰሪው ከሥራ ያሰናበተው ስለመሆኑ የማስረዳት ሸክም ያለበት ስለመሆኑ
በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ትዕዛዝ የተሰጠበት ተከራካሪ ወገን ፍ/ቤቱ ለጉዳዩ የመጨረሻ ውሣኔ ከመስጠቱ በፊት አቤቱታው ሊስተናገድ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 7ዐ(ሀ) 78 69 72
በአስፈፃሚ አካላት የሚወጡ የተለያዩ መመሪያዎች በነጋሪት ጋዜጣ ታትመው የወጡ ወይም በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጁ አለመሆናቸው ህጋዊ ውጤት እንዳይኖራቸው የሚከለክል ስላለመሆኑ አዋጅን መሠረት በማድረግ የወጡ መመሪያዎችን የሚፃረር ድርጊት መፈፀም በኃላፊነት ሊያስጠይቅ የሚችል ስለመሆኑ
ዳኝነት እንደገና እንዲታይ (Review of judgment) በሚል የሚቀርብ አቤቱታ አስቀድሞ በተሰጠ ውሣኔ ላይ ይግባኝ የተባለበት ነው በሚል ምክንያት ብቻ ውድቅ ሊደረግ የማይገባ ስለመሆኑ (ከዚህ ቀደም በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጉም የተለወጠ ስለመሆኑ) የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 6(1)(ሀ),(ለ)
ተከራካሪ ወገኖች ባላነሱበት ሁኔታ ፍ/ቤት የውል አፃፃፍ ሥርዓትን (ፎርማሊቲን) መሠረት በማድረግ በግራ ቀኝ ወገኖች መካከል የተካሄደን ውል ፈራሽ ነው በሚል የሚሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1723 1808(2)
በወንጀል ጉዳይ ተከስሶ ጥፋት የሌለበት መሆን በራሱ በተመሳሳይ ጉዳይ በፍትሐብሔር ከቀረበ ክስ ነፃ ለመውጣት እንደ በቂና የመጨረሻ መስፈርት የሚወሰድ ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2149
በተከራካሪ ወገኖች የሚቆጠሩ ማስረጃዎች ሳይሰሙ የሚቀሩት ለተያዘው ጉዳይ አግባብነት የሌላቸው መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ስለመሆኑ ፍ/ቤቶች ተከራካሪ ወገኖች የቆጠሩትን ማስረጃ ሳይሰሙ ወደ ጐን በመተው አቤቱታቸውን በበቂ ማስረጃ አላስረዱም በሚል የሚደርሱበት መደምደሚያ አግባብነት የሌለው ስለመሆኑ
መንግስታዊ የሆነ ተቋም በሚከሰስበትም ሆነ በሚከስበት ክርክር የሚቀርብ ሰነድ የኘሮቶኮል ቁጥር እንዲሁም ስለአቤቱታው ጽሁፍ ትክክለኛነት በሚመለከተው ኃላፊና በወኪሉ መፈረም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 8ዐ 92 93 እና 92(3)
በሌላ ሰው ድካም ወይም የሌላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አላግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠንና ባደረሰው ጉዳት መጠን ኪሣራ ሊከፍል የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2162
የውርስ ንብረት በጨረታ እንዲሸጥ ለማድረግ መነሻ ዋጋን ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1083 1084
በፌዴራል መንግስት የተመዘገበ የንግድ ማህበር (ድርጅት) ጋር በተያያዘ የሚነሣ ክርክርን ለማስተናገድ ስልጣን የተሰጠው ለፌዴራል ፍ/ቤቶች ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 25/88 አንቀፅ 5(6)
ከሳሽ የሆነ ወገን ክስ ለማቅረብ ምክንያት የሆኑትን ሁሉ በአንድ ላይና በአንድ ጊዜ አጠቃሎ ለመክሰስ የሚችል (የሚገባው) የነበረ ቢሆንም ሊጠይቅ ይገባው ከነበረው ቀንሶ ያቀረበው በፍ/ቤት ፈቃድ የሆነ እንደሆነ የቀረው መብት ላይ በድጋሚ ክስ ለመመስረት የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216(4)
ከውርስ ሃብት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የውርስ ሃብቱን በእጅ አድርጐ በመገልገል ላይ ያለ ተከራካሪ የሆነ ወራሽ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ንብረት በጋራ ይዞ የቆየ ሰው ላይ የሚያነሳው የውርስ ጥያቄ በይርጋ ታግዷል ሊባል የሚችልበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ
አንድ ተከሣሽ በተፈፀመ ወንጀል ላይ ተካፋይ ነበር ለማለት ተከሣሹ በሙሉ ፈቃዱና ዕውቀቱ በወንጀል ድርጊቱ ተሣታፊ የነበረ መሆኑ መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 33 63ዐ 25
አሠሪ የሆነ ወገን የሥራ ቅልጥፍናን፣ ውጤታማነትን፣ የኢንዱስትሪ ሰላምን ወይም ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት አንድን ሠራተኛ የተቀጠረበትን ደመወዝና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች በጠበቀ ሁኔታ አዛውሮ ለማሰራት የሚችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀጽ 2 (1) 4
የጉዲፈቻ ስምምነት የሕፃናትን ጥቅምት ለማስጠበቅ ሲባል ሊፈርስ የሚችል ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 195(2)
ባንክ በመያዣ መልክ የያዘውን የተበዳሪ ንብረት በአዋጅ ቁ. 97/9ዐ መሠረት በመሸጥ ላይ እያለ በሌላ በኩል ደግሞ በተበዳሪው ላይ በፍ/ቤት ክስ መስርቶ ዕዳው እንዲከፈለው ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ
Page 67 of 116