federal proclamations, regulations, directives, regional constitutions and laws.
You can search cases by number, volume, subject matter
Training and teaching materials, articles, legal forms, links to resources...
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 2ዐ8 መሠረት በሥር ፍ/ቤት የተደረገ እርማትን መነሻ በማድረግ የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አስቀድሞ የሰጠውን ውሣኔ ለመለወጥ የሚያስችለው የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 208 209 320 (1) ,348(1)
Download Cassation Decision
የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ በፍርድ ቤት ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በውሳኔው ወቅት ንብረቱን በእጁ አድርጐ የሚገኘው ወገን የንብረቱን ስመ ሐብት ወደ ሌላ ሦስተኛ ወገን አዛውሮ ሲገኝ ፍርድ ቤቶች ሊከተሉት ስለሚገባው አካሔድ
ለረጅም ጊዜ በመንግስት ቁጥጥር ሥር የነበረ ቤትን ይለቀቅልኝ በሚል አቤቱታ የሚያቀርብ ወገን ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይንም ከአዋጅ ውጪ ተወስዶብኛል የሚል ከሆነም ለሚመለከተው አካል ጥያቄውን አቅርቦ ውሳኔ አግኝቶ ባለመብትነቱን ሳያረጋግጥ የሚያቀርበው ክስ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ አዋጅ ቁጥር 47/67
በክረምት ወቅት የማስተማር ሥራ እንዲሠራ የሚያዝ ግልፅ ደንብ ወይም መመሪያ የሌለ እንደሆነ ወይም አስተማሪው በክረምት ወራት ለማስተማር የገባው የውል ግዴታ (ስምምነት) በሌለ ጊዜ በክረምት ወቅት ሥራን ለመስራት ፈቃደኛ አልሆነም በሚል ከሥራ ሊሰናበት የማይችል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 13(1)
በትዳር ወቅት የተወሰደ ብድር የአንደኛው ተጋቢ ፈቃድ የሌለበት ቢሆንም ፈቃዱን ያልሰጠው ተጋቢ የብድር ስምምነቱ እንዲፈርስ ያላደረገ እንደሆነ ወይም ደግሞ ለትዳር ጥቅም አለመዋሉን ማስረዳት ያልቻለ ከሆነ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የህግ ግምት የሚወሰድ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 68(መ)
ፍ/ቤቶች የቀረበላቸው አቤቱታ የክስ ምክንያት አለው ወይም የለውም ብሎ ለመወሰን በክስ ላይ የተገለፀው ነገር ቢረጋገጥ ከሳሽ የሆነው ወገን የጠየቀውን ዳኝነት ለማግኘት ህግ ይፈቅድለታል ወይስ አይፈቅድለትም የሚለውን ጥያቄ መመርመር ያለባቸው ስለመሆኑ
በተጭበረበረ መንገድ ወራሽነትን አሳውጆ የውርስ ንብረት አካል የሆነን ቤት ስመ ሃብት ወደ ራሱ አዙሮ የሚገኝ ሰው ጋር የሽያጭ ውል በተደረገ ጊዜ የሸያጭ ውሉ እንዲፈርስ በሚል ትክክለኛ ወራሾች የሚያቀርቡት ጥያቄ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍብ/ህ/ቁ. 2882 2884 997
ፍ/ቤቶች ለቀረበላቸው ክስ ምክንያት የሆነው ነገር መቋረጡን ወይም ጨርሶ መቅረቱን በክሱ ሂደት በማንኛውም ደረጃ በቂ በሆነ ማስረጃ በተገነዘቡ ጊዜ ክሱን ሊዘጉት የሚገባ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 280
የወለድ አግድ ውል ህጋዊ ነው ሊባል የሚችለው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ መቋቋምን የሚመለከቱ ድንጋጌዎችን በመከተል የተደረገ እንደሆነ ስለመሆኑና በዚህ መሰረት ያልተደረገ መሆኑ ውሉን ፈራሽ ሊያደርገው የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3118,3045,3052
ከእጅ በእጅ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ገዢ የሸያጩን ዋጋ የከፈለበትን ደረሰኝ ይዞ መገኘቱ የገዛውን ንብረት እንደተረከበ የሚያሳይ የመጨረሻ (conclusive) ማስረጃ ነው ሊባል የማይቻል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2266 2278(1) እና (2)
አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)
ፍ/ቤት ተከራካሪ ወገኖች ወለድን አስመልክቶ በውላቸው ካመለከቱት ሃሳብ ውጪ የራሱን ስሌት መሠረት በማድረግ ውሣኔ መስጠት ስላለመቻሉ የፍ/ብ/ህ/ቁ/. 1731 2478
በወንጀል ጉዳይ የቀረበ ክስ በዐቃቤ ህግ ምስክሮች ተሟልቶ አለመቅረብ የከሳሽ መዝገቡን የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆ መዘጋት በቀረበው ወንጀል ላይ ተፈፃሚ የሚሆነውን የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ ከመሆን የሚያግደው ስላለመሆኑ
የምትክ ወራሽነት ተጠቃሚዎችን ስለመለየት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 842,843,844(3)
በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሽ ስለሚጠየቅበት አግባብ የተመሰረተበት ክስ በዓቃቤ ሕግ በኩል እንደክሱ አመሰራረት ያልተረጋገጠበት ቢሆንም ተከሳሹ የቀረበው ማስረጃ ከቀረበበት ክስ ባነሰ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ተከሳሹ በነፃ እንዲሰናበት ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር /የሌለ/ ስለመሆኑ በከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከስሶ ጥፋተኛ መሆኑ የተረጋገጠ ተከሳሽ ስለሚጠየቅበት አግባብ የተመሰረተበት ክስ በዓቃቤ ሕግ በኩል እንደክሱ አመሰራረት ያልተረጋገጠበት ቢሆንም ተከሳሹ የቀረበው ማስረጃ ከቀረበበት ክስ ባነሰ የወንጀል ድርጊት የሚያስጠይቅ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ተከሳሹ በነፃ እንዲሰናበት ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የማይኖር /የሌለ/ ስለመሆኑ
ለተወሰነ ጊዜም ሆነ ላልተወሰነ ጊዜ የተቀጠረ ሠራተኛ ከውል ውጭ በሆነ ግንኙነት በሥራ ወቅት በሌሎች ሰዎች ላይ ለሚያደርሰው ጉዳት አሠሪ ኃላፊነት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2130 2131 2132
ከሥራ ክርክር ጋር በተያያዘ አሰሪ ሠራተኛው የፈፀመውን ድርጊት መሠረት አድርጐ ለማሰናበት የሚችለው የሥራ ውሉን ለማቋረጥ ምክንያት የሆነው ነገር መከሰቱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ በሚቆጠሩ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3)
በሸሪአ ፍ/ቤት በሚካሄድ ክርክር ላይ ጣልቃ ገብቶ መከራከር በፍ/ቤቱ ለመዳኘት ስምምነትን እንደመስጠት የሚያስቆጥር ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 188(92) አንቀፅ 5(1)
የልጆች ቀለብ አከፋፈል ሁኔታ ጋር በተያያዘ ክፍያ ተግባራዊ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ
Page 69 of 116