federal proclamations, regulations, directives, regional constitutions and laws.
You can search cases by number, volume, subject matter
Training and teaching materials, articles, legal forms, links to resources...
የደረሰን ጉዳት ከመካስ ጋር በተገናኝ በንግድ ህጉ እውቅና ስለተሰጣቸው የመድን ሽፋን (የኢንሹራንስ ውል) አይነቶችና ባህሪያት ለንብረት የሚሰጥ የኢንሹራንስ ሽፋን አደጋው በደረሰበት ጊዜ ንብረቱ የነበረውን ዋጋ ለመካስ የሚያስችል መሆን ያለበት ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁ. 654(2)(3),657, 674, 675, 688, 665, 678, 681, 680
Download Cassation Decision
ውል አዋዋይ ወይም ዳኛ ፊት የተደረገ ኑዛዜ በህጉ የተመለከተውን የኑዛዜው መነበብ ሥርዓትን ያላሟላ ከሆነ ህጋዊ ፎርማሊቲን የሚያሟላ እንደሆነ ለመቁጠር የማይቻል ስለመሆኑ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ 881(2), 882, 857
ከፍርድ አፈፃፀም ጋር በተገናኘ የሚንቀሳቀስ ንብረት የሀራጅ ሽያጭን አስመልክቶ ተፈፃሚነት ያላቸው የሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎች የሚንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የተካሄደ ጨረታ ሊፈርስ የሚችልበት አግባብ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.432-438, 445
ከባልና ሚስት የጋራ ንብረት ጋር በተገናኘ በጋብቻ ወቅት በአንደኛው ተጋቢ አማካኝነት ከባንክ ወጪ ተደርጐ ለ3ኛ ወገን የተላለፈ (የተሰጠ) ገንዘብ ለትዳር ጥቅም እንደዋለ የሚገመትበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 85-93
ከቅጅና ተዛማጅ መብቶች ጋር በተያያዘ የፊልም ባለቤት ለመሆን በማሰብ በባለሃብትና ፊልሙን ለመስራት በሚል በተደረገ ስምምነት መነሻነት ፊልሙን ለህዝብ ከማቅረብ ጋር ተያይዞ ጉዳዩ በፍ/ብሔር ክርክር ተደርጐበት በተሰጠ ውሣኔ መሰረት ፊልሙን በእጅ አድርጐ መገኘት በወንጀል ተጠያቂነት የማያስከትል ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.410/96 አንቀፅ 7(1)(ሀ), 36(1) የወ/ህ/ቁ.23(2), 57-59
በከሳሽነት የተሰየመ ወገን አንድ ንብረት በአንድ ህጋዊ ተግባር ሳቢያ ወደ እጄ ገብቷል በይዞታዬ ላይ እያለ ሁከት ተፈጠረብኝ በሚል የሚያቀርበው የሁከት ይወገድልኝ አቤቱታ በእርግጥም ሁከት ተፈጥሯል አልተፈጠረም የሚል ጭብጥ በመያዝ ሊስተናገድ የሚገባ እንጂ ክርክር የተነሣበት ንብረት በከሳሹ እጅ እንዴት እንደገባ ወይም ወደ ከሳሹ እጅ ሊገባ የቻለበትን ህጋዊ ተግባር ለመመርመር የሚያበቃ ምክንያት የሌለ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1149
ባንክ ለሰጠው ብድር በመያዣነት የያዘውን ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ንብረቶች አሻሻጥ ቅደም ተከተል ጋር በተገናኘ አቤቱታ ሊቀርብበትና ፍ/ቤቶችም ውሣኔ ሊሰጡበት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ97/90 አንቀፅ 7, 6 አዋጅ ቁ.216/92
በአሰሪው በኩል የተመቻቸን የውጪ የትምህርት እድል ተጠቃሚ በመሆን በምትኩ ለተወሰነ ጊዜ ለማገልገል ከተደረገ ውል ጋር በተገናኘ ሠራተኛው በውሉ ያለበትን ግዴታ እንዲወጣ ከሚጠበቅበት ጊዜ በፊት ከአሰሪው ፈቃድና እውቅና ውጪ ለሌላ ትምህርት ወደ ሌላ አገር በመዛወር የመጀመሪያው ውል ውጤት እንዳይኖረው ያደረገ እንደሆነ ሠራተኛው በውሉ የተመለከተውን ግዴታ ለመፈፀም እንዳልቻለ የሚያስቆጥረው ስለመሆኑ
በብልጫ የተከፈለ ቀረጥና ታክስ ተመላሽ እንዲሆን የሚቀርብ ጥያቄ ተቀባይነት የሚኖረው ዕቃው የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት አጠናቅቆ ወደ አገር ውስጥ ከገባበት ወይም ወደ ውጪ አገር ከተላከበት ቀን ጀምሮ በስድስት ወር ውስጥ የቀረበ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ፣ ""የጉምሩክ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቀቀ"" ማለት ስለሚቻልበት አግባብ አዋጅ ቁ.622/2001 አንቀጽ 66(1), 2(17),66(29),66(2)
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ክፍፍል ጋር በተገናኘ አንድን የጋራ ንብረት በዓይነት ለመካፈል ተጋቢዎቹ ከስምምነት ላይ ለመድረስ ያልቻሉ እንደሆነና ሁለቱም የቅድሚያ ግዢ መብት ጥያቄ ያቀረቡ እንደሆነ ንብረቱ ለጨረታ ቀርቦ እንዲሸጥ በማድረግ ገንዘቡን መካፈል ያለባቸው ስለመሆኑ፣ የደቡብ ብ/ብ/ሕ/ብ/መ/ የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 75/96 አንቀጽ 103(1)
አንድ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እንዲፈርስ ለመጠየቅ በቂና ህጋዊ መስፈርቶች መሟላታቸው መረጋገጥ ያለበት ስለመሆኑ፣ የማህበር ሥራው በአግባቡ አልተመራም ከሚል ጥያቄ ጋር በተያያዘ አግባብነት ያለው አካል የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ወይም ሌሎች አግባብነት ያላቸውን ህጐች መሠረት በማድረግ እንዲስተካከል ለመጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ፣ የንግድ ህግ ቁጥር 217, 218, 511, 543
Page 93 of 116