federal proclamations, regulations, directives, regional constitutions and laws.
You can search cases by number, volume, subject matter
Training and teaching materials, articles, legal forms, links to resources...
ተከራካሪ ወገኖች ጉዳያቸውን በእርቅ ለመጨረስ የተሰማሙና ይሄንኑም ስምምነት ለፍ/ቤት በማቅረብ ያስፀደቁ በሆነ ጊዜ ስምምነቱ እንደ ፍርድ ቤት ውሣኔ ተቆጥሮ መፈፀም ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 277
Download Cassation Decision
አስቀድሞ የተደረገ ነገር ግን ባለመታደሱ ምክንያት የተቋረጠ (ያበቃ)ን የመድን ውል መሠረት በማድረግ ሊጠየቅ የሚችል የጉዳት ካሣ ስላለመኖሩ የንግድ ህግ ቁ. 666(2) እና (3)
የግልግል ዳኝነት ጉባኤ እንደ ፍ/ቤት የዳኝነት አካሄድ ሁልጊዜ ጥብቅ የሆነ የሙግት ሥርዓትን ተከትሎ ጉዳዩን ማየት የሌለበት ስለመሆኑ የግልግል ጉባኤ ጉዳዩን ለማየት ሊከፈል የሚገባውን የገንዘብ መጠን በተመለከተ ተገቢ ነው ብሎ ያመነበትን ያህል ሊወስን ስለመቻሉ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 318/5/, 317/1/ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 3345
ወደ ሥራ እንዲመለስ ፍርድ የተሰጠ እንደሆነና በአሰሪው ችግርም ሆነ በሠራተኛው ፍላጐት በፍርዱ መሠረት ወደ ሥራ ለመመለስ ሠራተኛው ያልፈለገ ከሆነ ሠራተኛው የአሰሪና ሠራተኛ አዋጅ በምትክነት በሰጠው መብት መሠረት በመመለሱ ፈንታ ካሣ እንዲከፈለው አፈፃፀሙን ለያዘው ችሎት ጥያቄውን ባቀረበ ጊዜ ሊስተናገድ የሚገባው ስለመሆኑ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 43(3)
መጥሪያ በጋዜጣ ጥሪ ሊደረግ የሚገባው ሌሎች አግባብነት ያላቸው የመጥሪያ አላላክ መንገዶች ቅደም ተከተላቸውን በጠበቀ መልኩ ከተከናወኑ በኋላ ስለመሆኑ መጥሪያ በአግባቡ ደርሷል ለማለት የሚላክለት ሰው ስም በተሟላ ሁኔታ ተገልጾ መላክ ያለበት ስለመሆኑ መጥሪያ በህጉ አግባብ እንዲደርሰው ሳይደረግ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ ትዕዛዝ የተሰጠበት ወገን ትዕዛዙ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተገቢነት ያለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 94-110, 7870/ሀ
ኑዛዜ መኖሩን የማስረዳት ሸክም (ግዴታ) የተጠቃሚዎች ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 896,897
በአሰሪና ሠራተኛ ህጉ ‹‹… ውሉ የሚቋረጥበት ምክንያት መከሰቱን ካወቀበት…›› በሚል የተመለከተው ሃረግ ሊተረጐም የሚችልበት አግባብ አዋጅ ቁ. 377/96 አንቀፅ 27(3)
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418 አቤቱታ እንዲያቀርብ ተፈቅዶለት ክርክር ተካሂዶ ውሣኔ የተሰጠበት ወገን በድጋሚ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 447 ”ን” መሰረት በማድረግ የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 418, 447, 354
ለዋስትና የተያዘ ገንዘብን የአስያዡን ማንነትን ማረጋገጥ እስከተቻለ ድረስ ገንዘቡን ያስያዘበት ደረሰኝ ኮፒን ያቀረበ እንኳን ቢሆን የተያዘው ገንዘብ መመለስ ያለበት ስለመሆኑ
በዋናው ክርክር ላይ በተሰጠ ፍርድ መብቱ የተነካበት ሰው በፍርድ አፈፃፀም ወቅት መብቱ ከተነካበት ሰው በተለየ ሥነ ሥርዓት ተቃውሞ ማቅረብ የሚገባው ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 358, 418, 419
ከወንጀል ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥፋተኛ የተባለ ተከሳሽ የዘወትር ፀባይ መልካም የነበረ መሆኑ በተናጠል (በራሱ) ቅጣትን ለማቅለል የሚያስችል ስለመሆኑ የወንጀል ህግ ቁጥር 82(1) (ሀ)
በፍ/ቤቶች ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከር ትዕዛዝ የተሰጠው ተከራካሪ ወገን ጥሪ ተልኮለት ቀርቦ መልሱን አልሰጠም በሚል ምክንያት ከክርክሩ ውጪ እንዲሆን የሚሰጥ ትዕዛዝ በክርክሩ ውስጥ ያሉ ሌሎች ወገኖችን መብት የሚያጣብብና የሥነ-ሥርዓት ህግን የሚጥስ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ. 70, 41/3/, 199
እቃን ለመግዛት በጨረታ ማስታወቂያ ያወጣ ድርጅት ተወዳዳሪዎች በጨረታ ላይ ከተነገረው የተለየን ዕቃ በማቅረብ ከተወዳደሩ በኋላ ድርጅቱ ተወዳዳሪ የሆነው አካል በጨረታ ሰነዱ ላይ ሞልቶ ያቀረበውን እቃ መሰረት በማድረግ ውል የተዋዋለ እንደሆነ ይህንኑ ውል ለመፈፀም የሚገደድ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1695/2/
የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆነ ሰው የድርጅቱን አስተዳደራዊ ሥራ ለሌላ ሰው የወከለ መሆኑ ድርጅቱ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት በመፈፀም ወንጀል ጥፋተኛ በተባለ ጊዜ ከሚቀርብበት የወንጀል ተጠያቂነት ነፃ የማያደርገው ስለመሆኑ
ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ዕለት ለመቅረብ ያልቻለው በቂ ሊባል በሚችል እክል /ችግር/ ምክንያት መሆኑን ያስረዳ ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩ እንዲታይ በሚል የተሰጠው ትዕዛዝ እንዲነሳለት የሚያቀርበው አቤቱታ ተቀባይነት ያለው ስለመሆኑ “በቂ ምክንያት” በሚል የሰፈረው ሃረግ ሊተረጐም የሚገባው ተከሳሹ ቀና ልቦና ያለው መሆኑንና የተለያዩ አግባብነት ያላቸው ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ስለመሆኑ
በባህር ላይ እቃ አመላላሽ በእቃዎች ላይ ለደረሰ ጉዳት በኃላፊነት ሊጠየቅ ስለሚችልበት አግባብ፣ በባህር ላይ እቃን ለማመላለስ የውል ግዴታ የገባ ወገን ከእቃዎቹ መጐዳት ጋር በተያያዘ ስላለበት የኃላፊነት አድማስና ከኃላፊነት ነፃ ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የባህር ህግ ቁ.196,138,205,197,180(3)
አግባብነት ካለው የመንግስት አካል ፈቃድ ሳይኖር የከርሰ ምድር ቁፋሮ ሥራን ለመስራት የሚደረግ ውል ህጋዊና አስገዳጅ ሊሆን የማይችል ስለመሆኑ
በማህበር አባላት ስምምነት የሚወጣ ደንብን አስመልክቶ በማህበሩ አባላት መካከል ብሎም በማህበሩ እና በአባላት መካከል የሚነሱ አለመግባባቶችን እልባት ለመስጠት በፍትሐብሔር ህጉ ውስጥ ስለ ውሎች በጠቅላላው የተመለከቱት ድንጋጌዎች ተፈፃሚ ሊሆኑ የሚችሉ ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1676/1/
Page 77 of 116