federal proclamations, regulations, directives, regional constitutions and laws.
You can search cases by number, volume, subject matter
Training and teaching materials, articles, legal forms, links to resources...
አንድ ባለሙያ በአሠሪው ቁጥጥር ሳይሆን በራሱ የሙያ ኃላፊነት የሙያ አገልግሎት ለመስጠት ከአንድ አሠሪ ጋር ውል ሲኖረው ጉዳዩ የሚገዛው በአሠሪና ሠራተኛ ህግ ስላለመሆኑ፣
-ከአንድ ባለሙያ ጋር የሙያ ግልጋሎት ውል ያለው አሠሪ ውሉን በማናቸውም ጊዜ ማፍረስ ሥለመቻሉ፣
101890 labor law dispute termnination of contract of apprentice አንድ አሠሪ ለሙከራ የቀጠረውን ሠራተኛ በቀጠረው በ46ኛው ቀን ለስራው ብቁ አይደለም ብሎ የስንብት ደብዳቤ ቢጽፍለት ድርጊቱ ህገ ወጥ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ...
አንድ አሠሪ ለሙከራ የቀጠረውን ሠራተኛ በቀጠረው በ46ኛው ቀን ለስራው ብቁ አይደለም ብሎ የስንብት ደብዳቤ ቢጽፍለት ድርጊቱ ህገ ወጥ ነው ሊባል የማይችል ስለመሆኑ፣
አዋጅ ቁጥር 377/96 አንቀጽ
ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ሊባልባቸው ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች ጋብቻ በሁኔታ ፈርሷል ተብሎ ከሚታሰብበት ጊዜ አንስቶ በአስር ዓመት ጊዜ ውስጥ የንብረት ክፍፍል ጥያቄ ካልቀረበ በይርጋ የሚታገድ ስለመሆኑ
የሰ/መ/ቁ.102662
የካቲት 15 ቀን 2008 ዓ/ም
ዳኞች፡-አልማው ወሌ ዓሊ መሐመድ ተኽሊት ይመሰል እንዳሻው አዳነ ቀነዓ ቂጣታ
አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ለሼ- ጠበቃ ኤርሚያስ ደስታ ቀረቡ፡፡ ተጠሪ፡- አቶ በቀለ በላቸው- ወኪል
በተሻሻለው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የቤተሰብ ህግ መሰረት ባልና ሚስት የጋራ ንብረታቸውን እኩል የማስተዳደር መብት ያላቸውና የጋራ ስምምነት ሳይኖር ንብረትን ለሌላ 3ኛ ወገን በአንደኛው ተጋቢ ፍቃድ ብቻ የተላለፈ ከሆነና ይህንን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ በህጉ በተፈቀደለት ጊዜ ገደብ ውስጥ የይፍረስልኝ ጥያቄውን ካላቀረበ የተፈፀመው ተግባር እንደፀና የሚቆይ ስለመሆኑ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 68፣69
የሰ/መ/ቁ. 103721
የካቲት 03 ቀን 2008 ዓ.ም
አንድ ጋብቻ ሲፈርስ ንብረት ክፍፍልን በሚመለከት በእርቅ ውል ስምምነት በሽማግሌ የተደረገው እርቅ በፍ/ቤት ተመዝግቦ ከተዘጋ በኋላ እንደገና እንደ ባልና ሚስት አብረን እየኖርን ስለነበር በድጋሚ የንብረት ክፍፍል ይደረግ የሚል ጥያቄ አግባብነት ያለው ስላለመሆኑ፣
የሰ/መ/ቁ. 105054
ታህሳስ 22 ቀን 2008ዓ/ም
ዳኞች፡- ተሻገር ገ/ስላሴ
ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ተጠቃሚ ሆነው ባሉበት ፍቺ ቢከሰት የጡረታ መብት ተጠቃሚ የሆነው ባል ወይም ሚስት የጡረታ አበል ለባል ወይም ለሚስት ሊያካፍል የሚገባ ስላለመሆኑ ፣ የመንግስት ሠራተኞች ጡረታ አዋጅ ቁጥር 345/95 አንቀጽ 35
Download Cassation Decision
የገጠር መሬት እንደሌላው ንብረት በመቁጠር ከቤተሰብ ህጉ አንጻር የሚታይ ስላለመሆኑ ፣ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር በአንድ ተጋቢ ስም ተዘጋጅቶ ከተሰጠ በኋላ ጋብቻ ቢፈፀምና ተጋቢዎቹ መሬቱን የጋራ ለማድረግ ሊስማሙ የሚችሉ ስለመሆኑ፣ የአማራ ክልል የገጠር መሬት አጠቃቀም አዋጅ ቁ. 133/1999 አንቀጽ 24/3/ ደንብ ቁ. 151/1999 አንቀጽ 20/6/
የመጀመሪያ ሚስት በንብረትዋ ላይ ስምምነት ባላደረገችበት ፤ባል ሁለተኛ ሚስት ሲያገባ መቃወሚያ አላቀረበችም በማለት በንብረትዋ ላይም ስምምነት አድርጋለች በማለት በመደምደም ፤ሁለተኛ ሚስት እኩል እንድትካፈል በማለት የሚሰጥ ውሳኔ ህጋዊ ስላለመሆኑ
የባልና ሚስት የጋራ ንብረት ነው የተባለ ንብረትን አፈፃፀምን በተመለከተ የንብረቱ ሕጋዊነት ላይ የሚመለከተው አስተዳደር አካል አግባብ ያለው ውሣኔ እስኪሰጥ ድረስ መሸጥ መለወጥ ባይቻልም ባለበት ሁኔታ የግራ ቀኙን እኩል ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ አግባብ በጋራ የሚያስተዳድሩበት ወይም ተከፋፍለው የሚጠቀሙበት ወይም አከራይተው ጥቅሙን እኩል የሚከፋፈሉበት ሁኔታ መመቻቸት ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ 386/2/
ባ ል እና ሚስት በጋራ ሲጠቀሙበት የነበረ መሬት ጋብቻው በአንደኛው ተጋቢ ሞት የተቋረጠ ቢሆንም ሌላኛው ተጋቢ በሌላ ህጋዊ ምክንያት መብቱ እስካልተቋረጠ ድረስ ይዞታው በስሙ ተመዝግቦ ደብተር ለማግኘት እና በይዞታው ለመጠቀም የሚችል ስለመሆኑ፣ ሴቶች መሬትን በመጠቀም፤በማስተላለፍ፤በማስተዳደርና በመቆጣጠር ረገድ ከወንዶች ጋር እኩል መብት ያላቸዉ ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ሕ/መ አንቀጽ 35/7/፣ የኦሮሚያ የገጠር መሬት አዋጅ ቁ. 130/99 አንቀጽ 6/3/ እና ደንብ ቁጥር 151/2005 አንቀጽ 15
በባልና ሚስት የንብረት ክፍፍል ክርክር ወቅት ድብቅ የጦር መሳሪያ መኖሩ እስከተረጋገጠ ድረስ በሕግ አግባብ ስልጣን ባለዉ አካል አለመመዝገቡ መሳሪያዉ የለም የሚያስብል ሳይሆን የኢኮኖሚ ጥቅም ያለዉ እና ባልና ሚስት በትዳር እያሉ ያፈሩት እስከሆነ ድረስ ከሚመለከተዉ አካል ተመዝግቦ መሳሪያዉን ለመያዝ ፈቃድ አለመሰጠቱ፣ የተጋቢዎቹ የጋራ ሀብት እንዳይሆን የማያደርገዉ ስለመሆኑ የአማራ ክልል የቤተሰብ ሕግ አዋጅ ቁጥር 79/1995 አንቀጽ 73 (1) እና 101
Download
ጋብቻ በፍቺ ውሳኔ መፍረሱን ተከትሎ በንብረት ክርክር ወቅት የግል ዕዳ ነዉ ተብሎ ውሳኔ ያገኘ ዕዳ ፍ/ቤት ቀርቦ ባልተለወጠበት ሁኔታ በባለዕዳው ተጋቢ በኩል ለመጣው እዳ ሌላኛው ተጋቢ ተጠያቂነት የሌለበት ስለመሆኑ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 34 (1)፣ የፌደራል የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 57፣ 70፣ 71፣ 89 እና 93
የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658 ተጋቢ ወገን ከሦስተኛ ወገን ጋር ያደረገውን ውል ለማፍረስ ምክንያት ስላለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 658, 686
Cassation Decision no. 28663
ከጋብቻ በፊት የግል የነበረን ንብረት መነሻ በማድረግ በጋብቻ ጊዜ በግብይት የተገኘ ንብረት የግል ሆኖ ሊቀጥል የሚችለው በፍ/ቤት ቀርቦ የፀደቀ እንደሆነ ብቻ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 58(2) 57 62(2)
የአንደኛው ተጋቢ ስምምነት ሣይኖር የጋራ የሆነ የማይንቀሣቀስ ንብረት በሌለኛው ተጋቢ የተሸጠ እንደሆን ስምምነቱን ያልሰጠው ተጋቢ ካወቀበት ቀን ጀምሮ በ 6 ወር ውስጥ እንዲሁም በማናቸውም ሁኔታ ደግሞ በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ለመጠየት ስለመቻሉ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 69(2)
በጋብቻ ውል ላይ ባልና ሚስት “መተዳደሪያችን” ነው በሚል ያመለከቷቸው ንብረቶች የጋራ ንብረት ተደርገው የሚቆጠሩ ስለመሆናቸው
አንድ ወንድ ሁለት ሚስቶች ጋር ተጋብቶ በሚገኝ ጊዜ የንብረት ክፍፍል ሊደረግ የሚችልበት አግባብ የፌዴራል የተሻቫለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ. 213/92 አንቀጽ 102(1),86(1),62(1),63(1) የአማራ ብ/ክ/መ/የቤተሰብ ህግ አንቀጽ 113(1),97(1),73(1),74(1)
በባልና ሚስት የጋራ ንብረት ላይ የተደረገ የሽያጭ ውል በሕጉ በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ አለመፍረሱ ስለሚያስከትለው ውጤት
ከኮንዶሚኒየም ቤት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ከጋብቻ በፊት በአንደኛ ተጋቢ በተደረገ ምዝገባ የተነሣ የቤት ዕጣው የወጣው ብሎም የቤት ሽያጭ ውል የተደረገው በጋብቻ ወቅት መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ለቤቱ መገኘት ምክንያት የሆነው ተጋቢ ቤቱ የግል መሆን አለበት በሚል የሚያቀርበው ክርክር ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 62(2)
የጋብቻ ፍቺን በተመለከተ በፍ/ቤት የተሰጠ ውሣኔ ከሌለ በስተቀር የባልና ሚስት የጋራ ንብረትን አስመልክቶ የፍቺ ውጤት የሆነውን የክፍፍል ጥያቄ በፍ/ቤት ማቅረብ አይቻልም ለማለት የሚያስችል የህግ አግባብ የሌለ ስለመሆኑ የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ አዋጅ ቁ.213/92 አንቀፅ 76
Page 2 of 3