የአንድ ባለሙያ ማስረጃ በቀረበ ጊዜ በዋናነት የሚመረመረው የባለሙያው ገለልተኛነት እና ሙያዊ ብቃት ሲሆን ሁለቱን መስፈርቶች ካሟላ ማስረጃው የፍሬ ነገሩን መኖር ወይም አለመኖር ለማረጋገጥ ከፍተኛ ግምት የሚሠጠው (high probative value) ማስረጃ በመሆኑ ለባለሙያ ማስረጃ ውጤት ሳይሰጥ ውጤቱን አለመቀበል የማስረጃ ምዘና መርህ ስህተት ስለመሆኑ
በአንድ በተዘረጋ የኤሌክትሪክ መስመር ምክንያት ለደረሰ ጉዳት ኃላፊነቱን የሚወስደው የኤሌክትሪክ መስመሩን የዘረጋው አካል እንጂ ሌላ ሰው በቤቱ በዘረጋውና ባለቤት ላልሆነበት የኤሌክትሪክ መስመር አጥፊ ሳይሆኑ ኃላፊ ስለመሆን በተደነገገው የውል ውጭ ኃላፊነት ክፍል ኃላፊ ሊሆን የማይገባው ስለመሆኑ
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2066 – 2086