የአክሲዮን መተላለፍ ገዥና ሻጭን ለማስገደድ በጽሁፍ መደረግ ያለበት ሲሆን ማህበሩን ለማስገደድና የተላለፈለት ሰዉ በባለአክሲዮንነት ሙሉ መብት ለመጠቀም ስለአክሲዮን መተላለፉ ማህበርተኞች የተስማሙበት ዉሳኔ በአክሲዮኖች መዝገብ ሊመዘገብ የሚገባው ስለመሆኑ
የአክሲዮኖች መተላለፍ በ3ኛ ወገን ላይ መቃወሚያ ሊሆን የሚችለዉ ስለአክሲዮኖች መተላለፍ ዉል ሲኖር ወይም ማህበርተኞቹ የአክሲዮኖችን መተላለፍ ተቀብለዉ የተስማሙበት ሰነድ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት ተረጋግጦ መመዝገቡ ሳይሆን የአክሲዮኖቹ መተላለፍ በንግድ ሚኒስቴር የአክሲዮኖች መዝገብ ላይ ሲመዘገብ ስለመሆኑ
የንግድ ሕግ አንቀጽ 522 እና 523 /3/