አስቀድሞ በተደረገ የኪራይ ውል መነሻነት አንድን የአከራይ ንብረት ይዞ ሲጠቀም የቆየ ተከራይ የኪራይ ውል ግዜው ካለቀበት ጊዜ ጀምሮ አከራዩ የኪራዩን ዋጋ በመጨመር አዲስ የኪራይ ዋጋ እንዲከፈል ገልፆ እያለ ተከራዩ በቀረበው አዲስ የኪራይ ዋጋ ሳይስማማ ወይም እየተቃወመ በንብረቱ መገልገሉን በቀጠለ ጊዜ ተከራይ ለአከራዩ ሊከፍለው የሚገባውን የኪራይ ዋጋ ለመወሰን የሚቻልበት አግባብ፣ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2950(1) (2), 1687