ከጡረታ መብት ጋር በተገናኘ በሠራተኞች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለማየት ስልጣን ያለው አካል የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ተቋም ስለመሆኑና በኤጀንሲው ውሣኔ ቅር የተሰኘ ሠራተኛ ቅሬታውን ለማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ የማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ የሚሰጠው ውሣኔ በፍሬ ነገር ረገድ የመጨረሻ ስለመሆኑና በውሣኔው መሠረታዊ የህግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ቅሬታ ያለው ሠራተኛ አቤቱታውን ለፌ/ጠ/ፍ/ቤት በይግባኝ የማቅረብ መብት ያለው ስለመሆኑ፣ አዋጅ ቀ. 714/2003 አንቀጽ 56(1) (4), 57