ልዩ የውክልና ስልጣን ለመስጠት በተዘጋጀ ሰነድ ላይ ልዩ ውክልና ስለመስጠት በተመለከተ አግባብነት ያላቸው የህግ ድንጋጌዎች ያለመጠቀስ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ የአስተዳደር አካል የሆነ ተቋም በአንድ ወቅት የሰጠውን የፅሁፍ ማስረጃ በሌላ ጊዜ ማስተካከሉ በአንድ ጉዳይ ላይ ሁለት የተለያዩ ሰነድ ቀርቧል በሚል እንደማስረጃ ሰነድ ዋጋ የሚያጣበት አግባብ የሌለ ስለመሆኑ፣ በውክልና ሰነድ ላይ ለተወካይ የተሰጠው ስልጣን በይዘቱ ልዩ ውክልና የሚያመለክት ሆኖ ሰነዱ ስለ ልዩ ውልክና አስፈላጊነት የተቀመጠውን የፍ/ብ/ህ/ቁ 2208 ያለመጥቀሱ ብቻ ለተወካዩ ልዩ የውክልና ስልጣን እንዳልተሰጠ የሚያስቆጥር ስላለመሆኑ፣ ከሰነድ ማስረጃ ተቀባይነት ጋር በተያያዘ የሚነሣ ጥያቄ የህግ ጥያቄ በመሆኑ በሰበር ችሎት ሊስተናገድ የሚችል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2205, 2005(1), 2179, 2199, 2203, 2204